Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ሲዳማ ቡና የሊጉ ዋንጫውን የማንሳት ጥሩ ዕድል አለው” ጫላ ተሺታ (ሲዳማ ቡና)


የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ተስፋ ሰጪው የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች ጫላ ተሺታ ቡድናቸው ዘንድሮ በያዘው አቋም በጣም ደስተኛ መሆኑን እና
የሊጉንም ዋንጫ ሊያነሱ የሚችሉበት እድል እንዳላቸው አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ባለፈው ዓመት የተቀላቀለው እና ዘንድሮ ደግሞ የመጫወት እድልን ባገኘባቸው ጨዋታዎች ላይ ለክለቡ ጥሩ
በመንቀሳቀስ ተስፋ ሰጪን እንቅስቃሴ ሲያሳይ የነበረው ይኸው ተጨዋች በቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቱ ሲዳማን ለመጥቀም እና ለሀገሩ ብሔራዊ
ቡድን ለመመረጥም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም አስተያየቱን ጨምሮም ሰጥቷል፡፡
የሲዳማ ቡና እና ከዚህ በፊት ደግሞ ለኢትዮጵያ የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ የተጫወተውን ጫላ ተሺታን በኳስ ህይወቱ ዙሪያና ስለ ክለባቸው
እንደዚሁም ደግሞ የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳል በሚሉት ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው የሰጠን ምላሽ ይህንን ይመስላል፤ ተከታተሉት፡፡


-ስለውልደቱ እና እድገቱ
“የእኔ ውልደትና እድገት በሻሸመኔ ከተማ ቀበሌ 04 ውስጥ ነው፤ ልጅ ሆኜም በእዚያው አካባቢ ነው የእግር ኳስን በመጫወት ያደግኩት”፡፡
-የእግር ኳስ ተጨዋች ለመሆን ስለነበረው ፍላጎት
“የህፃንነት እድሜዬ ላይ ኳስን ስጫወት ወደፊት በክለብ ደረጃ ገብቼ ኳስ ተጨዋች እሆናለው በሚል ሙሉ ለሙሉ ፍላጎቱና ሃሳቡ ባይኖረኝም
በተወሰነ መልኩ ግን አስብ ነበር፤ በኋላ ላይም ይህ ተሳክቶልኝ ኳስ ተጨዋች ልሆን ቻልኩ”፡፡
-የእግር ኳስን ሲጫወት ቤተሰቡ ጋር ስለነበረው አመለካከት
“የእግር ኳስን ልጅ ሆኜ ስጫወት በቤተሰብ አካባቢ የነበረው አመለካከት እነሱ ትምህርት እንድማር ስለሚፈልጉ ኳሱን እንዳልጫወት ጫና
ያደርጉብኝ ነበር፤ ያኔ ጫና ስለነበረብኝም ነው ከላይ እንደገለፅኩት ወደፊት ኳስ ተጨዋች ስለመሆን ሙሉ ለሙሉ ሳስብ ያልነበርኩት”፡፡
-በቤታቸው ውስጥ የእግር ኳስን የሚጫወተው እሱ ብቻ ስለመሆኑ
“አዎን፤ የእግር ኳስን የእኛ ቤተሰብ ውስጥ የምጫወተው እኔ ብቻ ነኝ፤ 3 ወንድሞቼ እና አንድ እህቴ በትምህርት እና በሌላ የሙያ ዘርፍ ውስጥ
ነው የሚገኙት”፡፡
-የእግር ኳስ መጫወቱ ላይ መጀመሪያ ተሳትፎ ያደረገበት የሰፈር ክለብ
“የእግር ኳስን በታዳጊነት እድሜዬ ላይ በሰፈር ደረጃ ስጫወት መጀመሪያ የተጫወትኩበት ክለብ ሻሸመኔ በሚገኘው የካቶሊክ ሜዳ ላይ
የተጫወትኩበት ቡድን ነው፤ እዛም ተጫወትኩና ወደፕሮጀክት ተጨዋችነት ገባሁ”፡፡
-በክለብ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተበት

“ሻሸመኔ ከተማ ነው፤ እዛም የገባሁት ከፕሮጀክት ተጨዋችነቴ በኋላ ነው፤ ለቡድኑ መጀመሪያም በቢጫ ትሴራ ነው የተጫወትኩት፤ በጊዜው
በሜዳ ላይ ለቡድኑ ባሳየሁት ጥሩ እንቅስቃሴም ለኢትዮጵያ ወጣት ብሄራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ግርማ ሃ/የሱስ አማካይነት ለመመረጥ ብችልም
በጊዜው አንተ በእዚህ የእድሜ ደረጃ ለመጫወት ገና ነህ ተባልኩና በአሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ለሚመራው የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን እንድሄድ
ተደርጌ እዛ ልጫወት ችያለሁ”፡፡
የሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ እየተጫወትክ ይገኛል፤ ወደ ቡድኑ ስለገባህበት ሁኔታ እና ከክለቡ ጋር ስላለህ ቆይታ
“የሲዳማ ቡና ክለብን ልቀላቀል የቻልኩት የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ነው፤ ያኔ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራው ቡድን የተጨዋችነት ግዴታዬን ከተወጣሁ
በኋላ የሰበታ ከተማ ክለብ እኔን ፈልጎኝ ሊያስፈርመኝ ቢችልም ክለቡ ጋር በነበረኝ ቆይታ በራሴ የግል ምክንያት እነሱ ጋር ልቀጥል ስላልፈለግኩ
ከስድስት ወር በኋላ ነው ቡድኑን ለቅቄ ሲዳማን የተቀላቀልኩት፤ የሲዳማ ቡና ቆይታዬ ዘንድሮ ሁለተኛ አመቴን ነው፤ አምና ለቡድኑ አዲስ ፈራሚ
እንደመሆኔ ብዙ የመጫወት እድል አላገኘሁም፤ ይሄ ስለሆነም በእዚያው የውድድር ዘመን ላይ ለአዳማ ከተማ በውሰት ተሰጥቼ ተጫውቻለው፤
በአዳማም ጥሩ ጊዜም ስላሳለፍኩ በኋላ ላይ ንብረቱ ወደሆንኩለት የቀድሞ ክለቤ ዳግም በመመለስ ዘንድሮ ለቡድኑ ተቀይሬ በምገባበትም ሆነ
ተሰልፌ በምጫወትባቸው ጨዋታዎች ላይ ተስፋ ሰጪና አበረታች የሆነ እንቅስቃሴዎችን በክለቤ ውስጥ እያሳየው ነው የምገኘው”፡፡
የሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ ተሰልፈህ እንደተጫወትክ ሁሉ በቅርቡ ሜዳ ላይም አልተመለከትንህም ነበር
“አዎን፤ የሲዳማ ቡና ያደረጋቸው የቅርብ ጊዜ ጨዋታዎች ላይ ለቡድኔ በመሰለፍ ሳልጫወት ቀርቼ የነበርኩት ጎንደር ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር
ስንጫወት ጉዳትን አስተናግጄ ነበር፡፡ ለ15 ቀናት ያህልም ከሜዳ ርቄ ሶስት የሚደርሱ ጨዋታዎችን ስላደርግ ቀርቼ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን ከህመሜ
አገግሜ በጥሩ ጤንነት ላይ ስለሆንኩ የ18 ተጨዋቾች የስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘት ለቡድኔ መልካም የሆነ ውጤታማ ግልጋሎትን ልሰጠው ጥሩ
ሰአት ላይ ደርሼለታለው”፡፡
የሲዳማ ቡና የዘንድሮው የውድድር ዘመን ተሳትፎ በአንተ እይታ
“የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ላይ እያሳየ ያለው አቋም ጥሩ እና ሊደነቅለት የሚገባው ነው፤ ቡድኑ ራሱን በወጣት
ተጨዋቾች በመገንባት እና እያንዳንዱን ተጨዋች በከፍተኛ ፍላጎት እና ተነሳሽነትም ጭምር በማጫወት ወደፊት እየተጓዘም ያለ ቡድን ነው፤ የሲዳማ
ቡና አሁን ላይ የያዛቸው ተጨዋቾችም ክለቡን ለታላቅ ዉጤት ለማብቃት እየጣሩም ስለሆነ ስለሲዳማ ቡና ምርጥ እና ጥሩ ቡድንነት አፌን ሞልቼ
መናገር እችላለሁ”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ሲዳማ ቡና ስላለው እድል
“የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የዘንድሮውን የሊግ ዋንጫ ለማንሳት ያለው እድል ከሊጉ ቀሪ ጨዋታዎች አንፃር በራሱ እጅ ነው፤ ቡድናችን ከጥቂት
ግጥሚያ በስተቀር እንደ መቐለ 70 እንደርታና ፋሲል ከነማ ብዙም ፈታኝ ጨዋታዎች የሉትምና ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ በ5 ከተከታዩ ፋሲል
ከነማ በ3 ነጥብ ልዩነት ዝቅ ብለን የምንገኝ ከመሆናችን አንፃር የሊግ ዋንጫውን የማግኘት እድሉ እኛ አለን፤ ያ ባይሳካ እንኳን ሊጉን 2ኛና 3ኛ
ሆነን እናጠናቅቃለን፡፡
ለኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣት ብሄራዊ ቡድን ሲመረጥ ስለተሰማው ስሜት
“የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ኳስን ስትጫወት ከሁሉም በላይ ዋናው ደስታ ሃገርህን ወክለህ የምትጫወትበት እድልን ስታገኝ ነውና እኔም በታዳጊ
ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርጪ ስጫወት የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነበር፤ ይሄንን ወደፊት አጠናክሬ በማስጓዝም እስከ ዋናው
ብሄራዊ ቡድን በመመረጥ ሃገሬን ለማገልገል እፈልጋለሁ”፡፡
የእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ላይ ተምሳሌትህ ስለሆነው ተጨዋች
“የእግር ኳስ ተጨዋችነት ላይ የእኔ ተምሳሌት እና ሞዴሌ የሆነው ተጨዋች ሳላህዲን ሰይድ ነው፤ ከውጪዎቹ ደግሞ የማንቸስተር ሲቲው ራሂም
ስተርሊንግ ነው፤ የሁለቱ አጨዋወት ይስበኛል፤ አድናቂያቸው ነኝ”፡፡
የእግር ኳስ ሜዳው ላይ ስላለው ከፍተኛ ፍጥነት
“የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ስጫወትም ሆነ ከዚያ በፊት በነበረኝ የተሳካ የኳስ ህይወት በሜዳ ላይ ያለኝ ፍጥነት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
ይሄን ፍጥነት ላመጣው የቻልኩትም በትምህርት ቤት ደረጃ ስማር ሩጫን የሚያሰሩን አሰልጣኞች ነበሩና ያ ነው የጠቀመኝ”፡፡
ለፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ወደ ቱኒዚያ ካመራ በኋላ ዳግም ስለመመለሱ
“የኢትዮጵያ የታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች በነበርኩበት ሰአት ከግብፅ ታዳጊዎች ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ባሳየሁት ጥሩ እንቅስቃሴ የፕሮፌሽናልነት
ተጨዋችነት እድልን ከቱኒዚያው ክለብ ኢቶሃል ዶ ሳህል አግኝቼ ነበር፡፡ ከእኔ ውጪም የኢትዮጵያ ቡናው ሚኪያስ መኮንንም (ሚኪም) የእድሉ
ተቋዳሽ ነበርና ሁለታችንም ወደቱኒዚያ ክለብ ኢቶሃል ዶ ሳህል በማምራት እና ጥሩም የሙከራ ጊዜን በማሳለፍ ለአንድ ወር ከ15 ቀን ያህል ቆይታን
ብናደርግም ከክለቡ ጋር በኮንትራት ዙሪያ ልንስማማ ስላልቻልን ወደ ሃገራችን ልንመለስ ችለናል፡፡ የቱኒዚያው ክለብ እኛን በስሩ ለያዘው የወጣት
ቡድኑ ሊያቆየን የፈለገው የአምስት አመት ውል በማስፈረም ነው፤ ያኔ ታድያ ቡድኑ በፋሲሊቲ ደረጃ ሊያቀርብልን ካሰበው ውል አንፃር እዚህ
ሃገራችን ላይ የሚደረግልን ነገር ጥሩ ነው ብለን ስላሰብን ወደ ኢትዮጵያ ልንመለስ ችለናል፤ ያኔ የሆነውም ይሄ ነው”
በመጨረሻ
“ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጥቼ የአሁን ሰአት ላይ በክለብ ደረጃ እና ሃገሬን በምወክልበት ደረጃም ላይ በመገኘት ኳስን
እየተጫወትኩ መሆኔ በጣም ነው የሚያስደስተኝ፡፡ ኳስ ተጨዋች መሆን መቻልም መታደል ነው፤ ስለዚህም እኔን ለእዚህ ክብር ያበቁኝን አካላቶች
ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
የእግር ኳስን ከታዳጊነት እድሜዬ አንስቶ ስጫወት ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ ከእኔ ጎን ሆነው በማሰልጠንም ሆነ በመምክር የረዱኝን ቤተሰቦቼን
በፕሮጀክት ደረጃ ያሰለጠነኝን መስፍን በሻሸመኔ ያሰለጠነኝን ያሬድ አበጀን አሁን ላይ በሲዳማ ቡና የመሰለፍ እድሉን እየሰጠኝ እና እያሰለጠነኝ ያለውን
ዘርአይ ሙሉን እና ውዷ እናቴን ወ/ሮ ዘርፌ ፀጋዬን በጣም ማመስገን እፈልጋለሁኝ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P